=<({አል-ኢኽላስ 112:1-4})>=
ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ
1. በል! እርሱ አላህ አንድ ነው።
2. አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው።
3. አልወለደም፤ አልተወለደምም።
4. ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም።
![]() =<({አል-ቁርአን 96:1-5})>=
![]() በቡኻሪ በተዘገበው ሐዲስ መሰረት እውቀትን መሻት በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው። ![]() |
---|
ይህ ነው የዱንያ ሁኔታ ወደ ጣፋጭ ነገሮች ታመራለች ፤ ችግሮቿ ብዙ ናቸው ፤ ገፅታዋ ያስበረግጋል ፤ ሁሌም ትቀየራለች ፤ ጠራች ሲባል ትደፈርሳለች ፤ ከጭንቀት ጋር ተቀላቅላለች ሁሌም ታስተክዛለች።
አንድም ልጅ ሆነ ፣ ሚስት ፣ ጓደኛ ፣ የተከበረ ሰው ፣ ቤት ወይም ስራ አታገኝም የማያስደስት አንዳንዴም የሚያስከፋ ነገር ቢኖርበት እንጂ። ስለዚህ የመጥፎነቱን ግለት በጥሩ ጎኑ ቅዝቃዜ አብርደው።
አሏህ ይህች ህይወት ሁለት ተቃራኒ ነገሮችን ፣ ቡድኖችን ፣ ሃሳቦችን ፣ መልካምና መጥፎ ፤ ጥሩና ብልሹ እንዲሁም ደስታና ሀዘን እንዲኖራት ፈለገ። ከዚያም ጀነት ውስጥ መልካም ሁሉ ያለ ተቃራኒው ደስታን ጨምሮ ይኖራል። ተንኮል ፣ ጥፋትና ሃዘን ደግሞ እሳት ውስጥ ይሰባሰባሉ። በሐዲስም ውስጥ:-
«ዱንያ እርጉም ነች በውስጧ ያለውም ሁሉ የተረገመ ነው። አሏህን ማውሳትና የመሳሰሉት እንዲሁም አዋቂ እና የእውቀት ፈላጊዎች ሲቀሩ።»
ስለዚህ ህይወትህን እንዳለች ኑራት ፤ በምናቡም አለም ውስጥ አትንሳፈፍ። ዱንያህን እንዳለች ተቀበላት። ትኖርባትና ትረጋጋባት ዘንድ ራስህን አሳምን። እንደምትፈልገው በዚህች ህይወት ጓደኛ ከችግር አይጠራልህም ፤ ጉዳዮችም አይሟሉልህም ምክኒያቱም ጥራት ፣ ሙሉዕነትና ፍፁምነት መገለጫዋ አይደሉምና። ሚስትህ እንደምትፈልገው ላትሆንልህ ትችላለች። በሐዲስም:-
«አንድ አማኝ ከሚስቱ አይሽሽ ፤ አንድ ባህሪይ ቢጠላባት ሌላ ይወድላታልና»
ስለዚህ ትክክለኛ ለመሆን መጣር ይጠበቅብናል። ይቅርልንል ፣ የተገኘውን ልንቀበል ፣ የቸገረንን ልንተው ፣ አንዳንዴ እንዳላየን ልንሆን ፣ ጥፋቶችን ልናርምና አንዳንድ ነገሮችን እንዳላወቅን መሆን የግድ ይለናል።
የወጣቱ ተልዕኮ አድራሻ
ኢስላማዊ መጽሐፎችን ያውርዱ |
---|